በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

Posted 2020-10-26
Card image

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡


"የትምህርት ተቋማትን ሰላም ማስጠበቅ" በሚል ርዕስ የሰላም ሚኒስቴር ከፌዴራል ፓሊስ፣ ከኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ እና ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀና ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት በሰንዳፋ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ እየተሰጠ ይገኛል፡፡


መድረኩን በንግግር የከፈቱት በሰላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተዘግተው የነበሩትን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ለማስጀመር የፓሊስ አባላት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።


ወ/ሮ ፍሬአለም በሽታው እየተስፋፋ ከመሆኑም አኳያ ጥንቃቄ ማድረግ እና ግጭቶች እንዳይከሰቱ የሰራዊት አባላት ጠንክረው በመስራት የመማር ማስተማሩን ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።


የፓሊስ አባላት ጸጥታ ማስከበር ብቻ ሳይሆን የሚፈጠሩ ስህተቶችን ወደ ትምህርት በመቀየር መካሪም አስተማሪም እንዲሆኑ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Pictures


News

Card image
2020-11-03
ለመንግስት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
Card image
2020-10-30
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትኩረታቸዉ በተልዕኮአቸዉ ላይ መሆን አለበት ፤ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ
Card image
2020-10-30
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ ተመረቀ
Card image
2020-10-26
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
Card image
2020-10-22
Call for Journal Accreditation Application
Card image
2020-09-20
2021 Admission Application Information and Online Application Guide