የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትኩረታቸዉ በተልዕኮአቸዉ ላይ መሆን አለበት ፤ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ

Posted 2020-10-31
Card image

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትኩረታቸዉ በተልዕኮአቸዉ ላይ መሆን አለበት ፤

ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ

 

ዩኒቨርስቲዎች በየጊዜዉ መልካቸዉን እየቀያየሩ በሚመጡ አጀንዳዎች በመጠመድ ለተቋቋሙለት ዓላማ በሙሉ አቅማቸዉና ትኩረት እዳይሠሩ የሚያደርጉ ጉዳዮችን መቅረፍ መቻል እንደሚገባ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዛሬዉ ዕለት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲን በጎበኙበት ወቅት እንደገለፁት እንደ እኛ ሀገር በማደግ ላይ ያለ ኢኮኖሚ ዉጤታማና የለማ የሰዉ ሀይል በሁሉም ሴክተሮቻችን ስለሚያስፈልገን ዩኒቨርስቲዎቻችን ይህንን በሚያሳካ መልኩ የሰዉ ሀይል ልማት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስልግ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

 

በዉይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለዩኒቨርስቲዉ የሠላምና የልማት አማካሪ ምክር ቤት ባስተላለፉት መልዕክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም የመጣዉን ሀገራዊ ለዉጥ ተንተርሶ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችንን ሠላም ለማሳጣት የሚሠሩ ሥራዎችን በተደራጀ መንገድ ነቅተንና ተግተን መከላከል እንደሚገባ ለአባላቱ አብራርተዋል፡፡

ሠላም በመንግስት ጥረት ብቻ የሚረጋገጥ ስላልሆነ እንደ ዩኒቨርስቲ ላለፉት ዓመታት የጀመርናቸዉን ጥሩ ሥራዎች አጠንክረን የምቀጥል ከሆነ ምንም ችግር እንደማይፈጠርና ኮቪድን እየተከላከልን ሠላማዊ መማር ማስተማር እዉን እንደሚደረግ የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሠ ገልፀዋል፡፡

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በየደረጃዉ ያሉ አመራሮችና የዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ በጋራ የተናበበ ሥራ በመስራታቸዉ ዩኒቨርስቲዉ እጅግ በጣም በተሻለ ሁኔታ የመማር ማስተማር፣የምርምርና ሰፊ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን እየሠራ መሆኑን በዉይይቱ ላይ የተሳተፉት የዩኒቨርስቲዉ የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ደ/ር እንዲሪያስ ገልፀዋል፡፡

 

ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጉዳዮች ማብራሪያ የሠጡት ክቡር ሚኒሰትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንደ ከፍተኛ ትምህርት ሴክተርም ይሁን እንደ ተቋሞቻችን የእዉቀትና የቴክኖሎጂ ማዕከላት በማድረግ በህዝብ እና በሀገራዊ ፋይዳዎች ላይ አተኩረዉ እንዲሠሩ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች ከየትኛዉም ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ወጥተዉ በቂ እና ተወዳዳሪ የተማረ የሰዉ ሀይል እያመረቱ ዕድገታችን የሚፈልገዉን ችግር ፈቺ ተጨባጭ ምርምሮች ማድረግ ላይ ማተኮር እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

 

 

 

 

 Pictures


News

Card image
2021-02-15
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡
Card image
2021-02-12
የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ጥራትና አግባብነት ችግሮችን ለመሻገርና የዘርፉን የሪፎርም ስራዎች ለማሳካት የትምህርት አመራሩ የሀሳብና ተግባር ቅንጅት ያለዉና ተልዕኮን ማሳካት የሚችል መሆን ይገባዋል ተባለ፡፡
Card image
2021-01-11
The Minister highlights the importance of project delivery in line with the national policy frameworks.
Card image
2021-01-06
ለራያ ዩኒቨርስቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
Card image
2020-11-04
ለመንግስት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
Card image
2020-10-31
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትኩረታቸዉ በተልዕኮአቸዉ ላይ መሆን አለበት ፤ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ