በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ ተመረቀ

Posted 2020-10-31
Card image

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ ተመረቀ

ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሶስተኛ ካምፓስ የሆነዉ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ፣የሚኒስቴር መስሪቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣የደቡብ ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች የክልል የተለያዩ አመራሮች፣የወላታ እና ዳዉሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አመራሮችና የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል፡፡

በምርቃት ሥነስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ መንግስት የህብረተሰባችንን የልማት ጥያቄዎች አቅም በፈቀደ መልኩ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ በፍታሐዊነት ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ትምህርት፣ምርምር እና ሳይንሳዊ ባህሎችን እያጎለበትን መሄድ ሀገራችን ለምታደርገዉ የዕድገትና የብልጽግና ጉዞ የማይተካ ሚና ስላላቸዉ ዩኒቨርስቲዎቻችን ይህንኑ በዉል በመገንዘብ በትጋት መተግበር እንዳለባቸዉ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

ለፍትሐዊነትና ተደራሽነት የትምህርት ተቋማትን በምናስፋፋበት ወቅት ተቋሞቻችን ለትምህርት ጥራትም ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ መስራት እንደሚያስፈልግ ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡

የዳዉሮ ዞን ዋና ከተማ የሆነችዉ ተርጫ ከተማ ከወላይታ ሶዶ 170 ኪ.ሜ በላይ ርቃ የምትገኝ ስትሆን በዚህ ርቀት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በዳዉሮ ዞን ተጨማሪ ካምፓስ መክፈቱ የሁለቱን ዞኖች ህዝቦች በጋራ የመልማት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለዉ የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ሌሎች አከባቢዎችም ከዚህ መማር አለባቸዉ ብለዋል፡፡

Pictures


News

Card image
2021-02-15
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡
Card image
2021-02-12
የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ጥራትና አግባብነት ችግሮችን ለመሻገርና የዘርፉን የሪፎርም ስራዎች ለማሳካት የትምህርት አመራሩ የሀሳብና ተግባር ቅንጅት ያለዉና ተልዕኮን ማሳካት የሚችል መሆን ይገባዋል ተባለ፡፡
Card image
2021-01-11
The Minister highlights the importance of project delivery in line with the national policy frameworks.
Card image
2021-01-06
ለራያ ዩኒቨርስቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
Card image
2020-11-04
ለመንግስት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
Card image
2020-10-31
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትኩረታቸዉ በተልዕኮአቸዉ ላይ መሆን አለበት ፤ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ